Loading
Singer
የከበረውን ፡ ከተዋረደው ፡ ለይቼ ዐይኔ ፡ ተገልጦልኝ ፡ አምላኬ ፡ ያየልኝን ፡ አይቼ ለሕያው ፡ ተስፋ ፡ ተለይቼያለሁ ፡ ወስኜ ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ዓለማዊነትን ፡ ጨቅኜ በእውነት ፡ ተረትቻለሁ ፡ በእውነት ለሕይወት ፡ ተጠርቻለሁ ፡ ለሕይወት በፍቅር ፡ ተሸንፌአለሁ ፡ በፍቅር ለክብር ፡ ተለይቻለሁ ፡ ለክብር (እህም) ፡ መጐናጸፊያ ፡ ወድቆብኝ ፡ (እህ) ፡ እንድከተለው ፡ ጌታዬን (እህም) ፡ ሞፈር ፡ ቀንበሬን ፡ ሰብሬ ፡ (እህ) ፡ ጨክኜ ፡ ትቼው ፡ እርሻዬን (እህም) ፡ ምን ፡ ቀረኝ ፡ ብዬ ፡ ልመለስ ፡ (እህ) ፡ የያዝኩት ፡ ከእንቁ ፡ ይበልጣል (እህም) ፡ ሰው ፡ ክርስቶስ ፡ ተገልጦለት ፡ (እህ) ፡ ዓለምን ፡ እንዴት ፡ ይመርጣል አዝ፦ አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (አልመለስም) (፬x) በሆድ ፡ ሳልረሳ ፡ ከጥንቱ ፡ ያወቀኝ በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ሳለሁ ፡ የቀደሰኝ በአስደናቂ ፡ ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ አሸንፎ ተክሎኛል ፡ በቤቱ ፡ በምክሩ ፡ ደግፎ የዘለዓለሙን ፡ ተስፋ ፡ ጸንቶ ፡ የሚኖረውን በእጅ ፡ ያልተዳሰሰ ፡ የሰው ፡ ዐይን ፡ ያላየው ዋናዬን ፡ አግኝቻለሁ ፡ ከቶ ፡ አልመኝም ፡ ሌላ ዓለምና ፡ ምኞቱን ፡ አላይም ፡ ወደኋላ አዝ፦ አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ አልመለስም (አልመለስም) (፬x) የከበረውን ፡ ከተዋረደው ፡ ለይቼ ዐይኔ ፡ ተገልጦልኝ ፡ አምላኬ ፡ ያየልኝን ፡ አይቼ ለሕያው ፡ ተስፋ ፡ ተለይቼያለሁ ፡ ወስኜ ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ዓለማዊነትን ፡ ጨቅኜ በእውነት ፡ ተረትቻለሁ ፡ በእውነት ለሕይወት ፡ ተጠርቻለሁ ፡ ለሕይወት በፍቅር ፡ ተሸንፌአለሁ ፡ በፍቅር ለክብር ፡ ተለይቻለሁ ፡ ለክብር (፪x)