Loading
Singer
በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኢየሱሴ ፡ በላይ በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ሌላው ፡ ነገር ፡ አያስደንቀኝም ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ በቃ ፡ ተቀበለኝ ፡ በቃኝ በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ በቃ ፡ ዓለም ፡ በቃኝ (፪x) በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ ሊቀ ፡ ካህን ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ የመረጠኝ ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ አልተሳሳትኩም (፪x) ፡ በምርጫዬ ቀን ፡ ቆጠረና ፡ ዋጋ ፡ ከፈለኝ ፡ በተራዬ (፪x) ፍፁም ፡ ነው (፪x) ፡ ለእኔ ፡ የታየልኝ ፡ በጐ ፡ ስጦታው ልቤን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ከአብ ፡ ያገኘሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው መጽሐፉ ፡ ነግሮኛል ፡ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ ተቀምጠሃል ፡ ብሎ ከዚህ ፡ የበለጠ ፡ ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ዘንድሮ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ካለው (፪x) ፡ ትልቅ ፡ ነኝ ፡ ካለው በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል ፡ የተገለጠው (፪x) በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኢየሱሴ ፡ በላይ በዚህ ፡ ዓለም ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ሌላው ፡ ነገር ፡ አያስደንቀኝም ፡ ከኢየሱስ ፡ በላይ በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ በቃ ፡ ተቀበለኝ ፡ በቃኝ በቃ ፡ ጌታ ፡ አለኝ በቃ ፡ ዓለም ፡ በቃኝ (፪x) በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ ሊቀ ፡ ካህን ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ በቃኝ ፡ ነው ፡ ባሕር ፡ በአብ ፡ ቀኝ የመረጠኝ ፡ በሰማይ ፡ አለልኝ ክብርህን ፡ ያየሁ ፡ ዕለት ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ሞገስህን ፡ ሳየው ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ግርማህንም ፡ ሳየው ፡ ልቤ ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፍቅርህን ፡ ሳየው ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ባለ ፡ ግርማ ፡ ነህ (፪x) ፡ ባለ ፡ ግርማ ባለ ፡ ሞገስ ፡ ነህ (፪x) ፡ ባለ ፡ ሞገስ (፬x)