Loading
Singer
አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x) ቁስለኛውን ፡ ልቤን ፡ የሚጠግነው የነፍሴን ፡ ህመም ፡ የሚፈውሰው መንፈስህ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት በምድር ፡ ያለውን ፡ አይደለም ፡ ያየሁት የተሰበረውን ፡ አንተ ፡ የምትሻውን መስዕዋት ፡ አድርገህ ፡ የምታሸተውን ይህን ፡ መንፈስ ፡ ስጠኝ ፡ እለም ጸሎቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ እለምንሃለሁ አንተን ፡ የሚፈልግ ፡ ልብን ፡ ፍጠርልኝ የቀናውን ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ አድስልኝ ባክህን ፡ ጌታ ፡ ከፊትህ ፡ አትጣለኝ ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ (፫x) አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x) መንገዴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ያሳየኝ የሕይወቴ ፡ መሪ ፡ ለእኔ ፡ የሆነልኝ መንፈስህ ፡ ብቻ ፡ እረፍትን ፡ የሰጠኝ ከመከራ ፡ ስጋት ፡ እኔን ፡ ያሳረፈኝ ልክ ፡ እንደነኤልሳ ፡ እንደ ፡ ኤልያስ ልቤ ፡ ታዛዥ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ መንፈስ እንደ ፡ ወደድክ ፡ አርፈህ ፡ በእኔ ፡ እንድትሰራ ሕይወቴን ፡ ሰጠሁህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አደራ ብርና ፡ ወርቅ ፡ ለእኔ ፡ ሰላም ፡ አልሆነኝም ሃብትና ፡ ንብረትም ፡ እረፍት ፡ አልሰጠኝም ውስጣዊው ፡ እርካታ ፡ የልቤ ፡ ደስታ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰጠኸኝ ፡ ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ክበር ፡ ክብር ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ አለኝ ፡ የምለው ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ አንድም ፡ የለኝም ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ በላይ አልችልምና ፡ ያለአንተ ፡ መኖር መንፈስህ ፡ ሁሉ ፡ በሕይወቴ ፡ ይኑር (፪x)