Loading
Singer
የልብ ፡ ልቤን ፡ ላውጣው ፡ እስቲ ፡ ልናገር ጌታ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ የሚነገር እርሱ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ስሙኝ ፡ የሚነገር (፪x) የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ የራሴ መተኪያ ፡ የሌለህ ፡ ኢየሱሴ ከስንቱ ፡ ቦታ ፡ ስንቱን ፡ አሻግረህ ሊዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x) ፀሐዩ ፡ ሲጠልቅ ፡ ጨለማው ፡ ሲመጣ ንጉሥ ፡ ንጉሥን ፡ ሽሮ ፡ አንዱ ፡ በአንዱ ፡ ፈንታ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ጉልበቱ ፡ ሊፈታ የማትለዋወጥ ፡ የማትቀያየር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ(፪x) አለኸኝ ፡ የምለው የእኔው ፡ ነህ ፡ የምለዉ አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፪x) የልብ ፡ ልቤን ፡ ላውጣው ፡ እስቲ ፡ ልናገር ጌታ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ የሚነገር እርሱ ፡ ያደረገልኝ ፡ አለኝ ፡ ስሙኝ ፡ የሚነገር (፪x) የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ የራሴ መተኪያ ፡ የሌለህ ፡ ኢየሱሴ ከስንቱ ፡ ቦታ ፡ ስንቱን ፡ አሻግረህ ሊዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x) ወንዝ ፡ አያሻግርም ፡ የቅርብ ፡ ወዳጅ ፡ ሆኖ ፍቅር ፡ ዛሬ ፡ የለም ፡ ይላል ፡ ቀረ ፡ ድሮ ሁኔታ ፡ ሲለወጥ ፡ ከአለበት ፡ ቦታ የማትለዋወጥ ፡ የማትቀያየር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ(፪) አለኸኝ ፡ የምለው የእኔው ፡ ነህ ፡ የምለዉ አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፪x) አንተኑ ፡ አንተኑ ፡ ነዉ (፫x)