Loading
Singer
አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x) ሰዓቱ ፡ አይታወቅ ፡ መምጫው ፡ እንደ ፡ ሌባ ኮቴው ፡ አይሰማም ፡ ሲወጣ ፡ ሲገባ ድምፁ ፡ ሰው ፡ አይረብሽ ፡ አያውክ ፡ ጩኸቱ በድንገት ፡ ይሆናል ፡ የኢየሱስ ፡ መምጣቱ አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x) እንግዳ ፡ ጋብዤ ፡ ምንድነው ፡ መኝታ ለቀን ፡ ምሳ ፡ ልስራ ፡ እራቱን ፡ ለማታ ነቅቼ ፡ ልጠብቅ ፡ የሕይወቴን ፡ ጌታ ወገቤን ፡ አጥብቄ ፡ ልበል ፡ ማራናታ አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x) ላልዳኑ ፡ ልመስክር ፡ የዳኑትን ፡ ላፅና ትእዛዝ ፡ አልጠብቅም ፡ ተግባሬ ፡ ነውና ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ ላጥና ፡ በፀሎትም ፡ ልትጋ የገሃነምን ፡ ደጅ ፡ በስሙ ፡ ልዋጋ አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x) ሕይወት ፡ መቅኖ ፡ የለው ፡ ያልፋል ፡ እንደ ፡ ጤዛ ልቦናዬን ፡ ላጥራ ፡ እስኪ ፡ እራሴን ፡ ልግዛ ስለ ፡ ኀጢአቴ ፡ አምርሬ ፡ አለቅሳለሁ ለንስሐ ፡ ፆም ፡ እቀድሳለሁ አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x) የበደልኩትን ፡ ሰው ፡ ይቅርታ ፡ ልጠይቅ የበደለኝም ፡ ካለ ፡ ፈጥኜ ፡ ልታረቅ እርሾና ፡ እርም ፡ ይዜ ፡ መኖርም ፡ ይቅርብኝ ከፍቅር ፡ በስተቀር ፡ እዳ ፡ እንዳይኖርብኝ አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)