Loading
አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ እንደማንም ፡ ሰዉ አይወጣኝም ፡ ክፉ ፡ ቃልህ ፡ ጊዜ ፡ አለዉ እንደመልህቅ ፡ ይዞ ፡ አይለቀኝም ፡ ፍቅርህ ስጐዳብህ ፡ አይቶ ፡ ለካ ፡ አይችልም ፡ ልብህ (፪x) ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x) አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x) እንደሰው ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ አሰራሩ ከእለታት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አያበቃም ፡ ፍቅሩ መከራ ፡ እንደፈሳሽ ፡ ሲያልፍብኝ ፡ በላዬ ዘንበል ፡ አለ ፡ ፊትህ ፡ አየኸኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x) የአማልክት ፡ የጭፍሮች ፡ አምላክ ፡ ልመናዬን ፡ ሰምተኸው ፡ ደረስክ መኳንንቱ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ ፡ ውዴ ፡ ይግባ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ ያ ፡ መንፈሱ ፡ የመድሃኒቴ ፡ ይሰማኛል ፡ ገብቶ ፡ ከቤቴ አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x) አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ እንደማንም ፡ ሰዉ አይወጣኝም ፡ ክፉ ፡ ቃልህ ፡ ጊዜ ፡ አለዉ እንደመልህቅ ፡ ይዞ ፡ አይለቀኝም ፡ ፍቅርህ ስጐዳብህ ፡ አይቶ ፡ ለካ ፡ አይችልም ፡ ልብህ (፪x) ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x) አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x) የአማልክት ፡ የጭፍሮች ፡ አምላክ ፡ ልመናዬን ፡ ሰምተኸው ፡ ደረስክ መኳንንቱ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ ፡ ውዴ ፡ ይግባ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ ያ ፡ መንፈሱ ፡ የመድሃኒቴ ፡ ይሰማኛል ፡ ገብቶ ፡ ከቤቴ አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x) ተመስላሎ ፡ መኖር ፡ እያለ ፡ የሚቀለው ሞኝ ፡ ነው ፡ ቢሉኝም ፡ ሰዎች ፡ ሳይገባቸው ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ ልጠብቀው ፡ እሱን ሲፈልጓት ፡ ሲሿት ፡ ያዳነልኝ ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት ፡ ነፍሴን አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የኔ ፡ ሲሰማ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.