Loading
Singer
አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ አምላኬ ፡ ነህና እጅህ ፡ ሰርታኛለች ፡ ተመስገን እፍ ፡ ብለህብኝ ፡ እስትንፋስህን ሕያው ፡ ነፍስ ፡ ያለብኝ ፡ አደረከኝ ተመስገን ፡ አምላኬ ፡ አበጀኽኝ በእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ገና ፡ ሳለሁ በአንተ ፡ በአምላኬ ፡ ተለየሁ ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ላዳንከኝ ለውለታህ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋን ፡ አለኝ በመሰዋት ፡ ጻድቁን ፡ ልጅህን ገለጽክልኝ ፡ እኔን ፡ መውደድህን የእዳ ፡ ጽህፈቴን ፡ ደምስሰኽው ሕይወቴን ፡ የሞላው ፡ ምሥጋናህ ፡ ነው ህልናዬን ፡ በደምህ ፡ ቀድሰህ መንፈስክህ ፡ ሞላኸኝ ፡ እንዳመልክህ በቅዱሳን ፡ መሃል ፡ አቁመኸኝ የከበረን ፡ መዝሙር ፡ አዘመርከኝ በሥጋዬ ፡ ከከበኝ ፡ ሃጥያት አስጣልከኝ ፡ አድርገህልኝ ፡ ምህረት ታማኙና ፡ ኃይለኛው ፡ ክንድህ ፡ ታድጐኛልና ፡ ላመስግንህ በራሴ ፡ ስራ ፡ እኔን ፡ እያሳፈረክ ሽታዬን ፡ ጠረኔን ፡ እየቀይርክ በቃልህ ፡ ሰይፍ ፡ እየቆረጥከኝ ያለጠባስ ፡ ቁስሌን ፡ ፈወስከኝ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋን ፡ ለአንተ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ሰሪዬ ፡ ነህና