Loading
Singer
ሚያስፈልገኝን ፡ ያ'ረገልኝ ፡ ተንከባክቦ ፡ የሚያሳድገኝ የሚሸከመኝ ፡ እንደልጅነቴ ፡ አለልኝ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ (፪x) አዝ፦ አለኝ ፡ አባት ፡ አባት የምመካበት ፡ አባት አለኝ ፡ አባት ፡ አባት 'ማስፈራራበት ፡ አባት ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ወዴት ፡ ወዴት አትዘንጋው ፡ እንጂ ፡ አንዳለኝ ፡ አባት እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ፡ 'ሚያስብ ፡ 'ሚጠነቀቅ በልጁ ፡ የመጣበትን ፡ የማይምር ፡ የማይለቅ አዝ፦ አለኝ ፡ አባት ፡ አባት የምመካበት ፡ አባት አለኝ ፡ አባት ፡ አባት ማስፈራራበት ፡ አባት እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ እኩያ ፡ የለውም ግን ፡ እኮ ፡ ማንንም ፡ አይንቅም (፪x) ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ሁልጊዜ ፡ የሚምር መልካሙን ፡ መንገድ ፡ የሚያስተምር ማማክረው ፡ የሚመክረኝ አባቴ ፡ እያለ ፡ ምን ፡ አባዘነኝ ሰውን ፡ ተስፋ ፡ ማድረጉ ፡ በቃኝ ፡ በቃኝ ግራ ፡ ቀኝ ፡ ማየቱ ፡ በቃኝ ፡ በቃኝ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ መጥቼም ፡ ሸክሜን ፡ አራግፋለሁ ፡ ጌታ እንደማትሰለቸኝ ፡ ተማምኛለሁ ፡ ጌታ ሁልጊዜ ፡ የፍቅር ፡ ብሩህ ፡ ፊት ፡ አለህ ፡ ጌታ የሚያቀርብ ፡ የሚያስጠጋ ፡ ጌታ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልቆራኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ይሄ ፡ ነው ፡ የሚረባ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የሚበጅ (፬x) ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ