Loading
Singer
አለኝ ፡ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምታመነው ዘመን ፡ የማይሽረው ፡ ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፩) ሁሉ ፡ ሙሉ ፡ ሆኖ ፡ እጥፍ ፡ ቢኖረንም ለነፍሴ ፡ ጠበቃ ፡ ዋስ ፡ አይሆንልኝም ለኔ ፡ አለኝ ፡ የምለው ፡ ሁሉ ፡ የማመልከው አልፋማ ፡ ኦሜጋ ፡ ትልቅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ፪) ዝና ፡ ከበሬታ ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ነው አንድ ፡ ቀን ፡ ሲያበቃ ፡ ሁሉም ፡ አላፊ ፡ ነው በሰማይ ፡ ቢሆን ፡ ደግሞም ፡በምድር ለኔስ ፡ ድጋፍ ፡ አለኝ ፡ የማይሰበር አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ፫) ሰው ፡ ከማይገምተው ፡ ካልታሰበ ፡ ስፍራ በፍቅሩ ፡ ማረከኝ ፡ ክብሩን ፡ እንዳወራ ከሳሾቹን ፡ ሁሉ ፡ እያሳፈረልኝ አዲስን ፡ ዝማሬ ፡ በአፌ ፡ ጨመረልኝ አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ፬) ለሰይጣን ፡ ሽንገላ ፡ ጆሮዬን ፡ አልሰጥም ቢያወራ ፡ ቢያወራ ፡ ተስፋዬን ፡ አልጥልም ቢጐድልም ፡ ቢሞላ ፡ ጌታን ፡ አመልካለሁ ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ የሚበልጥ ፡ እርሱን ፡ እግኝቻለሁ አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)