Loading
Singer
አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x) ከኋላዬ ፡ ርቆ ፡ እንደ ፡ ህልም ፡ አለፈ እንደ ፡ ፈሳሽ ፡ ውኃ ፡ መጨነቄ ፡ ሄደ (፪x) ምሥጋናዬ ፡ አርጐ ፡ መቅደስህን ፡ ይሙላው ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ ይሄም ፡ ሲያንስብህ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x) እጅህ ፡ እየረዳኝ ፡ ሁሉን ፡ ተሻገርኩ አልገፋ ፡ ያለውን ፡ ቀኖቼን ፡ አለፍኩ (፪x) ለአደረከው ፡ ሥራ ፡ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ነፍስ ፡ ያለው ፡ ግዑዙ ፡ ወድቆ ፡ ይሰግድልሃል (፪x) አዝ፦ አልገፋ ፡ ያልውን ፡ ቀን ክንድህ ፡ ገፍቶት ፡ አሻገርከኝ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ መቸገሬን ፡ አስረሳኸኝ ማን ፡ ልበልህ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምላሽ ፡ አጣሁ ፡ ጌትዬ ፡ የምከፍልህ ፡ አዎ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ክብሬን ፡ ጥዬ ልስገድልህ ፡ ጌታዬ ፡ ተዋርጄ (፪x) ምን ፡ ቢሰጥህ ፡ ምላሽ ፡ የአንተን ፡ ሥራ ፡ ይተካል እንዲያው ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ ማመስገን ፡ ይሻላል (፪x) እስከ ፡ ምድር ፡ ዳርቻ ፡ የሚመስልህ ፡ ታጥቷል ትልቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ይገባሃል (፪x) የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ባለ ፡ ውለታ (፪x) ላብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ላብዛልህ ላብዛልህ ፡ ስግደትም ፡ ላብዛልህ (፪x) የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ባለ ፡ ውለታ (፪x) ላብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ላብዛልህ ላብዛልህ ፡ ስግደትም ፡ ላብዛልህ (፪x)