Loading
Singer
ስለማልችል ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር አትሂድብኝ ፡ ባክህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ እኔስ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ አልችልምና ችላ ፡ አትበለኝ ፡ ክብሬን ፡ ክብሬ ፡ ነህና አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ አይሆንልኝም ፡ እኔስ ያላንተ ፡ መኖር (፪x) ዓይኔን ፡ በእጄ ፡ አልወጋም ፡ የጠራኝን ፡ ትቼ እንዴት ፡ ነው ፡ ምኖረው ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ ሌላው ፡ ሚመካበት ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ነገር ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ አይሆንልኝም ፡ እኔስ ያለአንተ ፡ መኖር ሲከብደኝ ፡ ብቸኝነቴ ፡ ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ በቤቲት ቅዱሱን ፡ መንፈስ ፡ አልኩኝ ፡ እባክህ ፡ አትሂድብኝ የሰው ፡ ጥማቱ ፡ ሌላ ፡ ነው የኤኔ ፡ ግን ፡ አንድ ፡ ብቻ ፡ ነው ያላንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም ለአፍታ ፡ እንኳን ፡ አትተወኝ ስለማልችል ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር አትሂድብኝ ፡ ባክህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ እኔስ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ አልችልምና ችላ ፡ አትበለኝ ፡ ክብሬን ፡ ክብሬ ፡ ነህና ሳኦል ፡ ምን ፡ ነክቶት ፡ ከሰረ ለሥጋው ፡ ምቾት ፡ ስለአደረ አጥፋልኝ ፡ ብለህ ፡ ስትልከው ያማረውን ፡ ለኤራሱ ፡ አስቀረው በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ተታሎ በድፍረት ፡ ሲጓዝ ፡ አይ ፡ ብሎ ድምጽህን ፡ ንቆ ፡ ሲወጣ መንፈስህ ፡ ሸሽቶ ፡ ተቀጣ አጥፋልኝ ፡ ያልከውን ፡ አጠፋዋለሁኝ ሰዋልኝ ፡ ያልከውን ፡ እሰዋዋለሁኝ ዝክሩን ፡ ከምድር ፡ ላይ መንግሥቱን ፡ አፍርሼ አስደስትሃለሁኝ ፡ ቃልህን ፡ ጠብቄ አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ አይሆንልኝም ፡ እኔስ ያላንተ ፡ መኖር (፪x)