Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x) ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፩) በሰማይ ፡ የሚታይ ፡ ደመና ፡ ባይኖርም ንፋስም ፡ ባይኖርም ፡ አይዘንብም ፡ አልልም የተናገረኝን ፡ አልጠረጥረውም (፪x) እርሱ ፡ ይሆናል ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ አልልም አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x) ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፪) አላሳልፍ ፡ ብሎ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ቢሞላ ጉልበቴን ፡ ሊያላላ ፡ አላይም ፡ የኋላ የጠራኝን ፡ አምላክ ፡ ቃሉን ፡ አምነዋለሁ ፡ እታመነዋለሁ በእምነት ፡ ተሻግሬ ፡ በድል ፡ እቆማለሁ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x) ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፫) በጉልበቱ ፡ ጽናት ፡ የሚራመደው (፪x) አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ነው ከፍ ፡ ከፍ ፡ ቢያደርግ ፡ ሲያሻው ፡ ቢከለክል (፪x) በሚሰራው ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትክክል (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x) ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፬) አምላክህ ፡ ትቶሃል ፡ ጠላቴ ፡ ቢለኝም ቢነዘንዘኝም ፡ ይህ ፡ ለኔ ፡ አይገባኝም ምንም ፡ ቀን ፡ ቢገፋ ፡ ተስፋው ፡ ቢዘገይም አምላኬ ፡ ያለው ፡ ቃል ፡ መፈጸሙ ፡ አይቀርም አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x) ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው