Loading
Singer
ከህግ በታች ያለን - በተጣለ ስጋ እዳን የሚከፍል - የበቃን ፍለጋ ማን ያድነን ብለን - ስንጠብቅ ተዓምር ማህተሙን ፈቶ - በራሱ ሞት ‘ሚምር አላውቅም - ከሰው በደል በላይ አላውቅም - የሰው ድካም አሞት አላውቅም - በፅድቅ ሆኖ ሳለ አላውቅም - ለኃጥአን የሚሞት… ለካ ግን አለ - ስሙ ማይከስም ሞቶ የተነሳ - ሰማሁ አንድ ስም [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x ለገዛ ፍርዳቸው - ምትክ ልሁን ባለ ለሚሳለቁበት - መስቀል ላይ እንዳለ ላደረጉት ሁሉ - ምህረት የሚለምን አንዱን ብቻ ሰምተን - እንዲህ የተገረምን አላውቅም - እንዲህ ያለ ነገር አላውቅም - ድንቅ የሆነ ወሬ አላውቅም - በጆሮዬ አልገባም አላውቅም - ነበር እስከዛሬ…. ለካ ግን አለ - ባለይቅርታ ሰማሁ አንድ ስም - እንዲ ያለ ጌታ…. [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x ድኩም መስሎ መምጣት - ታላቅ ክብሩን ትቶ ክብርን ከጠገበ - አልጠብቅም ከቶ እንዴት ያለ ንጉስ - እንዴት ያለ ኃያል ሀይሉን በገዛ እጁ - ትቶ ፍዳን ያያል? አላውቅም - በዙፋን ላይ ሳለ አላውቅም - የደካማ ወዳጅ አላውቅም - ክብሩን ትቶ ሚወርድ አላውቅም - ያላንዳች አስገዳጅ.... ለካ ግን አለ - ለኛ የሚገደው አንድ ስም አለ - ፍርዱን የናደው... [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x