Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አላማዬ ፡ ነዉ (፪x) ጠላት ፡ የሚለኝን ፡ ለምንስ ፡ ልስማዉ ልውጣ ፡ ልሄድ ፡ ልውረሰዉ ፡ አዎ (፪x) አላማ ፡ ያላቸው ፡ የጥንት ፡ አባቶቼ ድል ፡ አደረጉ ፡ እንጂ ፡ ተሸነፉ ፡ መቼ እኔም ፡ አላማዬን ፡ አንተን ፡ አድርጌያለሁ የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ በእምነት ፡ እወርሳለሁ እወርሳለሁ ፤ እወርሳለሁ (፬x) አማሌቅ ፡ በፊቴ ፡ ሆኖ ፡ ቢያቅራራ ምን ፡ ትልቅ ፡ ቢመስል ፡ እኔ ፡ እንደው ፡ አልፈራ የአምላኬን ፡ ስም ፡ ይዤ ፡ በእምነት ፡ እወጣለሁ ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ አጋድመዋለሁ አምላኬ ፡ ሃይሌ ፡ ነው እኔ ፡ አልፈራም ፡ አልፈራም (፪x) እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አልሰጋም (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አላማዬ ፡ ነዉ (፪x) ጠላት ፡ የሚለኝን ፡ ለምንስ ፡ ልስማዉ ልውጣ ፡ ልሄድ ፡ ልውረሰዉ ፡ አዎ (፪x) እንደ ፡ ሰናኦር ፡ ግምብ ፡ ቢቆምም ፡ በፊቴ ይደባልቀዋል ፡ ቋንቋውን ፡ አባቴ ምርኮን ፡ በምርኮ ፡ ላይ ፡ ይጨምርልኛል ያመንኩት ፡ ጌታዬ ፡ መቼ ፡ ይተወኛል (፪x) እኔ ፡ አልፈራም ፡ አልፈራም (፪x) እኔ ፡ አልሰጋም ፡ አልሰጋም (፪x) የድል ፡ ሰንደቄ ፡ ነው ፡ የሕይወቴ ፡ አርባ ፡ አሃሃ እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታ ፡ ባለግርማ ባለግርማ ፡ ኢየሱስ ፡ ባለግርማ (፪x)