Loading
Singer
አላማዬ ፡ አይደለም ፡ እራስን ፡ ማስከበር አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ለታይታ ፡ መቅረብ አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ መታየት አላማዬ ፡ አይደለም ፡ በዓለም ፡ ታዋቂነት አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን አላማዬ (፬x) ዋሽቶም ፡ ሰርቆም ፡ መስሎም ፡ አጭበርብሮም ፡ ሊያሸንፈው ፡ ይታገላል ፡ ኑሮን ለሕሊናው ፡ ክስ ፡ ያስተባብላል ፡ ይሞታል ፡ ወይ ፡ ብሎ ፡ ያሳብባል የሰው ፡ ጭንቀት ፡ ለመኖር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ስለነገ ፡ ማሰብ ፡ ለከንቱ ፡ ነው ነገ ፡ ይጨነቅ ፡ ስለራሱ ፡ ብሎ ፡ አላማ ፡ አለኝ ፡ ከሁሉ ፡ አስበልጦ አላማዬ ፡ የከንቱ ፡ አይደለም አላማዬ ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ አላማዬ ፡ ስራ ፡ ፈት ፡ አይደለም አላማዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ስራ አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን አላማዬ (፬x) አላማዬ ፡ አይደለም ፡ እራስን ፡ ማስከበር አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ለታይታ ፡ መቅረብ አላማዬ ፡ አይደለም ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ መታየት አላማዬ ፡ አይደለም ፡ በዓለም ፡ ታዋቂነት አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን አላማዬ (፬x) እልፍን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወደኋላ ፡ የሚያይን ፡ ሰው ፡ አልሆንም ፡ ተላላ ከእንግዲህ ፡ ቀኝ ፡ ኋላ ፡ ዞሬ ፡ አልሄድም ፡ አላማዬን ፡ አውቃለሁ ፡ የያዝኩትን ኢየሱሴ ፡ ሁን ፡ የሞቴ ፡ ማምለጫ ፡ ተገደብኩኝ ፡ ከከንቱ ፡ እሩጫ ፍቅር ፡ የሆነው ፡ የርሱ ፡ አላማ ፡ ስለገባት ፡ ነፍሴም ፡ አታቅማማ አላማዬ ፡ የከንቱ ፡ አየደለም አላማዬ ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ አላማዬ ፡ ስራ ፡ ፈት ፡ አይደለም አላማዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ስራ አዝ፦ አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን አላማዬ (፬x) አላማዬ ፡ ለመኖር ፡ ነው ፡ አስከብሬው ፡ ኢየሱሴን አላማዬ (፵x)