Loading
Singer
ዛሬም ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ ዋይታ የዚህ ፡ ምድር ፡ ኑሮ ፡ የለውም ፡ እርካታ ጊዜው ፡ ሲደርስ ፡ ያኔ ፡ መምጫው ፡ የጌታዬ ፊት ፡ ለፊቴ ፡ ሳየው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ደስታዬ (፪x) አዝ፦ አላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x) ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x) ዘለዓለሜ ፡ በዚያ ፡ በክብር በአብ ፡ ቀኝ ፡ በደስታ ፡ ለመኖር በእርግጥ ፡ ናፍቄያለሁ ፡ ደርሳለሁ የታረደውን ፡ በግ ፡ መሲሁን ፡ አያለሁ (፪x) አዝ፦ አላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x) ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ በዚህ ፡ ምንም ፡ የለኝ ፡ የለኝ የሰው ፡ ዓይን ፡ ያላየው ፡ ያላየው በእጅ ፡ ያልተሰራው ፡ እርስቴ እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው ፡ የላይኛው ፡ ቤቴ (፪x) አዝ፦ አላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x) ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ የፍጥረት ፡ ሩጫ ፡ ሲገታ ለምድሩ ፡ በጊዜው ፡ ሲያበቃ ሙሽራው ፡ በድንገት ፡ ሲመጣ ፍጻሜን ፡ ያገኛል ፡ የቅዱሳን ፡ ተስፋ (፪x) አዝ፦ አላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x) ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)