Loading
Singer
አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x) እራሴን ፡ ሰውነቴን ፡ መሰዊያው ፡ ላይ ፡ ላኑርልህ ፡ አሃሃ ቅድስና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ሕያው ፡ መስዋት ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ (፪x) አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x) ከፍ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ተከብሮ ፡ ያለ ፡ በሠማይ ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት የማይመረመረው ፡ ድንቅ ፡ ነገር የማይቆጠረው ፡ ተዓምራት (፪x) ሁሉን ፡ ያደረገው ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ይህ ፡ የሰራ ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ አሃ (፪x) ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን (፬x) አላገኘሁም ፡ ፈልጌ ፡ ፈልጌ ለአንተ ፡ የምሰጠውን ፡ መስዋት ፡ አድርጌ (፪x) እራሴን ፡ ሰውነቴን ፡ መሰዊያው ፡ ላይ ፡ ላኑርልህ ፡ አሃሃ ቅድስና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ሕያው ፡ መስዋት ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ ኃይል ፡ የሌለውን ፡ ምንኛ ፡ ረዳኸው ጥበብ ፡ ያጣውን ፡ ምንኛ ፡ መከርከው የደከመውን ፡ ምንኛ ፡ አገዝከው የተጣለውን ፡ ምንኛ ፡ አነሳኸው (፪x) ረድኤቴ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ (፬x) የረዳኝ ፡ የረዳኝ ፡ ጌታዬ ባለውለታዬ ፡ ባለውለታዬ ፡ ባለውለታዬ (፪x) ሕይወቴን ፡ የሞላህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ ጉልበቴን ፡ ያጸናህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ ጽዋዬን ፡ የሞላህልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገንልኝ አንተ ፡ እጅህን ፡ ትከፍታለህ አሃ ፡ ትከፍታለህ ፡ ኦሆ ፡ ትከፍታለህ ሕይወት ፡ ላለው ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ ነገር ታጠግባለህ ፡ ኦሆ ፡ ታጠግባለህ ፡ አሃ (፪x) እንደገና ፡ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞላው ዓይኔም ፡ አየችው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው እንደገና ፡ እንደገና ፡ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞላው ዓይኔም ፡ አየችው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው (፫x) አምላኬ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው ህልም ፡ ነው ፡ ወይ ፡ እውን ፡ እንዴት ፡ ይገርማል እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ አንድ ፡ ቃል ፡ ያበቃል (፪x) ከፍ ፡ ያለው ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ተከብሮ ፡ ያለ ፡ በሠማይ ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት ምሥጋና ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት አምልኮ ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት ዝማሬም ፡ አይነስበት ፡ ክብርም ፡ ይጨመርለት