Loading
Singer
አዝ፦ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ ፍቅርህ ፡ ለይቶኛል የምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ አኑሮኛል ታዲያ ፡ከበርኩ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ከሰርኩኝ ፡ እኔ የዘላለም ፡ አምላክ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ (፬x) ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከጐኔ አዝ፦ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ ጠላት ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በተነሳ ፡ ጊዜ ነፍሴን ፡ ሊያስፈራራ ፡ ከቦኝ ፡ በትካዜ ኢየሱስ ፡ ደረስህልኝ ፡ አሳርፈኽኛል ስምህ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖ ፡ አስመልጠኸኛል (፬x) ዛሬ ፡ አድርሰኸኛል አዝ፦ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ ድንቅ ፡ ታምራትህን ፡ ማዳንህን ፡ እያየሁ ቃል ፡ ኪዳን ፡ አለብኝ ፡ አገለግላለሁ ገና ፡ የሚበልጥ ፡ አዲስ ፡ ክብር ፡ አለ ዛሬ ፡ ዓይኔ ፡ ከሚያየው ፡ ከዚህ ፡ የተሻለ (፬x) ሌላ ፡ ክብር ፡ አለ አዝ፦ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ