Loading
Singer
አኬልዳማ፦(፬x) የደም ምድር እግዚአብሔር ያስብሽ በርሱ ፍቅር አኬልዳማ፦(፬x) የደም መሬት እግዚአብሔር ያስብሽ በምህረት 1. የብዙ ሺህ ሠው ደም ጠጥተሻል ያም ቢሆን ግን አልረካ ብለሻል ዛሬሞ ትጠጫለሽ እንደውሃ በየዳር ድንበርሽ በበረሃ አኬልዳማ ... 2. እሾህ አሜኬላ አብቅለሻል አመፃና ክህደት አብዝተሻል በፍቅር በትር ነው የገረፈሽ ይቅርታን ለምኚው ተንበርክከሽ አኬልዳማ ... 3. ልጆችን በአደባባይ ፈጥፍጠሻል የአዛውንቶችን ራስ ቀጥቅጠሻል ፃድቃን አፈሰሱ የደም እንባ እርሱ ነው በእግዚአብሔር ጆሮ የገባ አኬልዳማ ... 4. ከአንድ ማህፀን የወጡ መንትያ ተቃቅፈው ያደጉ ባንድ ጉያ በጥይት ያጭዳሉ ሠው እንደሳር እግዚአብሔር ያስታርቅሽ ከራስሽ ጋር