Loading
Singer
አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x) ከማር ፡ ከወለላ ፡ ሁሉ ፡ የሚጣፍጠው ከነገሮች ፡ ሁሉ ፡ እጅጉን ፡ የሚበልጥ አለኝ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ የተከበረው ጌታም ፡ አጽንቶታትል ፡ የማይሻር ፡ ነው አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x) በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ አንተን ፡ እንዳመልክህ ጌታ ፡ በኑሮዬ ፡ ቃልህን ፡ አብራልኝ ከአመጸኛ ፡ ከንፈር ፡ ከሸንጋይ ፡ አንደበት ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጠብቀኝ ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ እንድኖር አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x) ባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ዝምም ፡ አትበለኝ ቃልህን ፡ አብራልኝ ፡ ከፊትህ ፡ አትጣለኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቃልህ ፡ ተስፋ ፡ አደርገዋለሁ በናፍቆት ፡ በጉጉት ፡ እጠባበቃለሁ አዝ፦ አካሄዴን ፡ ጌታ ፡ እንደቃልህ ፡ አቅና ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ደካማ ፡ ነኝና ቃልህ ፡ እጅግ ፡ የነጠረ ፡ ነው እንክርዳድን ፡ ከስንዴ ፡ የሚለይ ፡ ነው (፪x)