Loading
Singer
ለውድቀት ፡ መሮጤ ፡ ምንድነው ማዳንህ ፡ የገባኝ ፡ ጥንት ፡ ነው አባቴ ፡ ልጄ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ እያልከኝ የጎረቤት ፡ ኑሮ ፡ የናፈቀኝ ጥፋቱ ፡ ከጠላት ፡ ወይ ፡ ከኔ ገብቶኝ ፡ እንዳልገባው ፡ መሆኔ አመል ፡ ካልሆነብኝ ፡ በስተቀር አሁን ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ጠላት ፡ ሰፈር አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x) ማን ፡ አየኝ ፡ አላየኝ ፡ ኑሮዬን አልደብቀው ፡ ካንተ ፡ ገበናዬን ሰው ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ሸሽቶስ ፡ እስከመቼ ልኑር ፡ መጀመሪያ ፡ አንተን ፡ ፈርቼ እንዳልሞት ፡ ነበረ ፡ መዳኔ ፈቅደህ ፡ የሞትክልኝ ፡ ካህኔ እያወቅኩ ፡ ከገባሁ ፡ ከእሳቱ ማን ፡ ሊመልሰኝ ፡ ነው ፡ ማን ፡ ብርቱ አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x) ነጻነቴም ፡ በዛ ፡ መሰለኝ ምን ፡ አለበት ፡ ኑሮ ፡ ለመደኝ ቀለለኝ ፡ የጥፋት ፡ መንገዴ ላይቀርልኝ ፡ ካለፈ ፡ መንደዴ የማውቀውን ፡ እውነት ፡ ሳልገፋ ከበር ፡ መልስ ፡ ሳልሆን ፡ ሳልጠፋ ብላቴናነቴን ፡ ታደገው አውለው ፡ ከቤትህ ፡ ከሚበጀው አዝ:- አግዘኝ ፡ ደግፈኝ (ደግፈኝ) ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ (ብቻዬን----አቅም ፡ የለኝ) ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር (ያየህልኝን----ቁም ፡ ነገር) እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (እንዳላጣው----ተራ ፡ ነገር) (፪x)