Loading
Singer
አንድ ፡ ጉዳይ ፡ አንድ ፡ ነገር ሲወራ ፡ ቢዋል ፡ ሲተረክ ፡ ቢታደር የማያሰለች ፡ እውነት ፡ የሆነ ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ የተከወነ (፪x) አዝ፦ አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ ሞተልን ፡ ሳይራራ ፡ ለነፍሱ አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ንጉሡ እጆች ፡ ገረፉት ፡ የፈጠራቸው ተፉበት ፡ ጌታ ፡ ላይ ፡ መች ፡ ፀፀታቸው ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ጩኽቱስ ፡ ተሰማ የዓለሙ ፡ ጌታ ፡ ሆነ ፡ እንደ ፡ ደካማ ንጹህ ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ እንደወንጀለኛ በውርደት ፡ ሰቀሉት ፡ የሱስን ፡ ስለኛ መለኪያስ ፡ አለ ፡ ወይ ፡ ለዚህ ፡ ፍቅር ፡ መጠን እንዲሁ ፡ ወዶን ፡ እራሱን ፡ ለሰጠን አዝ፦ አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ ሞተልን ፡ ሳይራራ ፡ ለነፍሱ አጋፔ (፪x) ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እርሱ ፍቅሩ ፡ እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ንጉሡ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ፍቅር (፪x) የወደደውን ፡ ማንም ፡ ይወዳል መልካም ፡ ላረገ ፡ እርሱም ፡ ይክሳል የኢየሱሴ ፡ ግን ፡ የሚለየው ራሱን ፡ የሰጠ ፡ ለጠላ ፡ ነው የኢየሱሴማ ፡ የሚለየው ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ለገፋው ፡ ነው