Loading
Singer
የገባልኝ ፡ ኪዳን ፡ ልቤን ፡ እያስንሳው ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ (፪x) ከተሰቀለበት ፡ በገናዬን ፡ ቃኘሁ በአድደባባዮቹ ፡ እንዳምነው ፡ እንዳከብረው ሞኝ ፡ ነው ፡ ጠላቴ ፡ ይህንን ፡ ዘነጋ ጌታ ፡ ሳይለው ፡ ቀኔ ፡ እንደማይዘጋ አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማህሌት ፡ እቆማለሁ መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ በሞትና ፡ በእኔ ፡ መሃል ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ በጭንቅ ፡ ቀን ፡ የሚረዳ ፡ የሚያግዝ ፡ ጠፍቶ ዐይኖቼን ፡ ወደ ፡ ተራሮ ፡ እንኳን ፡ ባነሳ እያሞካሸ ፡ የጠራኝ ፡ ወዳጄን ፡ ልረሳ ቃሉን ፡ ልኮልኝ ፡ ከሰማይ ፡ ሃይሌን ፡ ያደሰው (ኦሆ) ውበት ፡ የሰጠው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ለፈራረሰው (ኦሆ) የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ መኖሪያ (አሃ) ልዘምር ፡ ሳላናጋግር ፡ ሳልሰማ ፡ ዙሪያ (ኦሆ) አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማህሌት ፡ እቆማለሁ መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ የገባልኝ ፡ ኪዳን ፡ ልቤን ፡ እያስንሳው ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ እያለኝ ቃል ፡ አለኝ ፡ ከሰማይ ፡ ኪዳን ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር ተስፋዬን ፡ አስቦ ፡ ሁሌ ፡ ልቤ ፡ ተረጋጋ ሃሳቡ ፡ ሳይሞላ ፡ ጠላቴ ፡ ሲሸበር ምሥጋና ፡ እና ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ በእኔ ፡ ሰፈር አዝ፦ አፌ ፡ ተሞላ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና ጥሩልኝ ፡ እስቲ ፡ ባለበገና በቦታዬ ፡ ላይ ፡ ማለት ፡ እቆማለሁ መቅደሱን ፡ በክብር ፡ አደንቀዋለሁ ዘምር (፫x) ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ ዘምርልኝ ፣ ዘምር ፡ እንጂ ፣ ዘምር ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ ዘምር (፫x) ፡ እያለኝ የጠራኝ ፡ መረጠኝ ፡ የጠራኝ ፡ በደስታ