Loading
Singer
የእውነት ፡ መልክ ፡ ያለው ፡ ከእውነት ፡ የተጣላ የጊዜውን ፡ ያየ ፡ የነገው ፡ ተላላ በሌላው ፡ ላይ ፡ ፈራጅ ፡ ጣቶቹን ፡ ቀሳሪ ስለእራሱ ፡ ኑሮ ፡ ሕያውን ፡ ቀባሪ ካባው ፡ የሸፈነው ፡ መቃብርነቱን የምላሱ ፡ ቂቤ ፡ አጥምዶ ፡ አረካለት የልብ ፡ አውሬነቱን አዝ፦ አድኅነነ ፡ ከመዐቱ ፡ ሰውረነ ፣ ስማነ ፡ አምላክነ ፡ ወመድኃኒነ (፪x) (ይቅርብኝ) ፡ ላይጠቅመኝ ፡ ይቅርብኝ (ይቅርብኝ) ፡ ቢቀርብኝ ፡ ሞት ፡ ነው (ይቅርብኝ) ፡ ለካ ፡ የተወዳጀኝ (ይቅርብኝ) ፡ ተንቀሳቃሽ ፡ ሞት ፡ ነው (ይቅርብኝ) ፡ የፍቅር ፡ ሰው ፡ መሳይ (ይቅርብኝ) ፡ የወንድም ፡ አታላይ (ይቅርብኝ) ፡ ስንቱን ፡ ወጥቶ ፡ ጣለው (ይቅርብኝ) ፡ ያልብሾት ፡ ተናኝ ታረቅ ፡ ከራስህ ፡ ጋር ፡ ወገኔ ሁሉ ፡ ያመልጥሃል ፡ ስትል ፡ ለእኔ ፣ መኖር ፡ ልመድ ፡ እንጂ ፡ ለሌላዉ ያ ፡ ነው ፡ የሕይወት ፡ ተድላ ፡ ደስታዉ ።(፪x) አዝ፦ አድኅነነ ፡ ከመዐቱ ፡ ሰውረነ ፣ ስማነ ፡ አምላክነ ፡ ወመድኃኒነ (፪x) ጣኦት ፡ ተሰይፎ ፡ መቅደሽን ፡ ይዘርፋል ሕሊናህን ፡ ጥሶት ፡ አካልህ ፡ ይሮጣል ልጓም ፡ አበጂለት ፡ ራስህ ፡ ከአንተ ፡ ወጥቷል ሁለት ፡ ሰው ፡ ሆነህ ፡ መታወቂያህ ፡ ጠፍቷል ሩቅ ፡ አሳቢ ፡ ሆነህ ፡ በቅርቡ ፡ አዳሪ የአፍ ፡ ብቻ ፡ አርበኛ ፡ አስጐምጅቶ ፡ በላ አንቱ ፡ ፈሪሳዊ እኔነቴን ፥ በእኔው ፡ ያለ ፡ የእኔው ፡ ጠላቴ ፣ አላወጣው ፡ ውስጤ ፡ በእኔው ፡ ነዋሪ ፡ ቤቴ ኖሮ ፡ እንዳያጠፋኝ ፡ ንቃልኝ ፡ ውስጠቴን (፪x) ማረን ፡ ማረን ፡ ይቅር ፡ በለን ስማን ፡ ስማን ፡ ተቀበለን (፪x)