Loading
Singer
አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር ለመድኃኒታችን ፡ ክብር የምሥጋናችንን ፡ ሽታ እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x) በእረኛቸው ፡ የታመኑ ፣ በመስኩ ፡ የተሰማሩ ዱካውን ፡ እየተከተሉ ፣ ለደህንነት ፡ የተጠሩ ከጨካኝ ፡ አውሬ ፡ የዳኑ ፣ ከመታረድ ፡ የተረፉ ሃሴትን ፡ እንደሚያደርጉ ፡ በአጥፊው ፡ ጥፋት ፡ ስላልጠፉ አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር ለመድኃኒታችን ፡ ክብር የምሥጋናችንን ፡ ሽታ እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x) ማቃችንን ፡ ቀዷልና ፡ ፀጋውን ፡ አልብሶናልና ክብራችን ፡ ትዘምርለት ፡ ፍቅሩ ፡ አጽናንቶናልና ጉዳታችንን ፡ የሚሹ ፡ ጉድጓድ ፡ ምሰው ፡ የጠበቁን አጋንንት ፡ አፍረዋልና ፡ ያደፈጡት ፡ ሊያጠቁን አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር ለመድኃኒታችን ፡ ክብር የምሥጋናችንን ፡ ሽታ እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x) በፍፁም ፡ ልብ ፡ እንዘምር ፣ በአምላካችን ፡ ደስ ፡ ይበለን እናጨብጭብ ፡ ዕልል ፡ እንበል ፣ ለምንስ ፡ እንቆጥባለን በምሥጋናችን ፡ ዝማሬ ፡ ምሽጉን ፡ እናፈርሳለን በመንፈሳዊው ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬን ፡ እንዘምር ለመድኃኒታችን ፡ ክብር የምሥጋናችንን ፡ ሽታ እናሳርግ ፡ በዕልልታ (፪x)