Loading
Singer
ታሪክ ፡ አይደል ፡ ተረት የሰራው ፡ በኔ ፡ ሕይወት ብዙ ፡ ሀያላን ፡ እያሉ ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ በቃሉ አዝ፦ አዳነኝ ፡ ወደደኝና ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ ፡ አወጣኝ አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ አስቤው ፡ አይደልም ፡ አቅጄ (፪x) አስቦልኝ ፡ እንጂ ፡ ተወድጄ (፪x) የሞት ፡ ወጥመድ ፡ ቀርቦ ፡ ሊይዘኝ ኪዳኑ ፡ ምህረቱ ፡ አዳነኝ (፪x) የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ለሚጠፉት ፡ ሞኝነት ለእኔ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ የመኖሬ/የመዳኔ ፡ ምክንያት አዝ፦ አዳነኝ (፪x) ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ እንደማልችል ፡ አውቆ ፡ በራሴ (፪x) ታዳጊ ፡ ሆነላት ፡ ለነፍሴ (፪x) ነጠቀኝ ፡ ከአፋፉ ፡ ከሞት (፪x) አረገኝ ፡ ካህኑ ፡ ለፍቅሩ ፡ መንግስት (፪x) አዝ፦ አዳነኝ (፪x) ፡ አስቀመጠኝ ፡ ጐኑ ፡ በአብ ፡ ቀኝ አዳነኝ (፪x) ፡ የመንግስቱ ፡ ወራሽ ፡ አረገኝ ታሪክ ፡ አይደል ፡ ተረት የሰራው ፡ ለኔ ፡ ሕይወት ብዙ ፡ ኃያላን ፡ እያሉ ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ በቃሉ አዝ፦ አዳነኝ ፡ ወደደኝ ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ሰፊው ፡ ስፍራ ፡ አወጣኝ አዳነኝ (፪x) ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግስት ፡ አገባኝ የመስቀሉ ፡ ቃል ፡ ለሚጠፉት ፡ ሞኝነት ለእኔ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ የመኖሬ/የመዳኔ ፡ ምክንያት (፪x)