Loading
Singer
ታላቅነትህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ የሚያበራ ድምጽህ ፡ ነጐድጓድ ፡ ነው ፡ የሚያስፈራ ደረትህን ፡ በወርቅ ፡ የታጠቀ እጅግ ፡ ያማረ ፡ ነው ፡ ውበትህ አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ እያደነቀ አቤቱ ፡ ሥራህን ፡ እያደነቀ ታላቅነትህን ፡ እያደነቀ ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ ይኸው ፡ አፈለቀ (፪x) እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ የቤትህን ፡ ስርዓት ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) አቤቱ ፡ ጥበብህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) የቤትህን ፡ ስርዓት ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) አቤቱ ፡ ጥበብህን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) ስለ ፡ አንተ ፡ ከሰማሁት ፡ ዝና ፡ ይልቅ በዓይኔ ፡ የማየው ፡ ሆነብኝ ፡ ድንቅ ስለዚህም ፡ ነፍሴ ፡ ተማረከች የምሥጋናን ፡ ዜማ ፡ አፈለቀች አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህ ፡ (አቤቱ ፡ ውበትህ) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ) አቤቱ ፡ ሥራህን ፡ (አቤቱ ፡ ሥራህን) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ) ታላቅነትህን ፡ (ታላቅነትህን) ፡ እያደነቀ ፡ (እያደነቀ) ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ (ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን) ይኸው ፡ አፈለቀ ፡ (ይኸው ፡ አፈለቀ) (፪x) እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ የእጆችህን ፡ ሥራ ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) አቤቱ ፡ ፍጥረታትን ፡ አይቼ ፡ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ (፪x) ጨረቃና ፡ ፀሐይ ፡ ከዋክብት በምድር ፡ ላይ ፡ ያሉ ፡ እንስሳት ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ለአንተ ፡ ተፈጥረዋል አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ሥራህ ፡ ያስደንቃል አዝ፦ አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ እያደነቀ (አቤቱ ፡ ሥራህ) ፡ አቤቱ ፡ ሥራህ ፡ እያደነቀ (ታላቅነትህን) ፡ ታላቅነትህን ፡ እያደነቀ ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገርን ፡ ይኸው ፡ አፈለቀ (፪x) እንደፈጣን ፡ ፀሓፊ ፡ አንደበቴን ፡ እከፍታለሁ መቼ ፡ ያስችለኛል ፡ አምላኬ ፡ ክብርህን ፡ እያየሁ አመሰግንሃለው ፡ አሃሃ ፡ አመሰግንሃለሁ ፡ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ፡ ኦሆሆ ፡ አመሰግንሃለሁ