Loading
Singer
በዙሪያዬ ሆኖ ጠላት ሲያውከኝ ያሸነፈ መስሎ ሲፎክርብኝ በጨነቀኝ ጊዜ ወዳንተ ጮህኩኝ ሰማይን ዝቅ አርገህ ከተፍ አልክልኝ አዝ: አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x) እጆቼን አንስቼ ተገፋው አልኩኝ እግዚአብሔር ከሰማይ ተበቀለልኝ ምድር ተናወጠች ቁጣውም ነደደ በጠላቶቼ ላይ መብረቅ አወረደ አዝ: አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x) እግሮቼም ቆሙልኝ አልተንሸራተቱም ጠላቶቼን ያዝኩኝ አላመለጡኝም በኮረብቶቹም ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ እስኪ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ አዝ: አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x) ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው ክፉዬን አይወድም ይነዳል ቁጣው ከመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ይሰማኛል እግዚአብሔርን አይቶ ጠላቴ ፈርቶኛል አዝ: አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የእኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x) አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ አቤቱ የኔ ጌታ እወድሃለሁ እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድኃኒቴ የምታመንበት ሆነኝ እረዳቴ (፪x)