Loading
Singer
አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x) በዘመን ፡ በአመታት ፡ ስራህን ፡ እየሰራህ የሚቃወምህ ፡ ሳይኖር ፡ ክንድህን ፡ እየገለጥክ ልጆችህን ፡ ከድል ፡ ወደ ፡ ድል ፡ እያሸጋገርካቸው የጠላታቸውን ፡ ሰፈር ፡ ይታያል ፡ . (1) . ፡ ወርሰው አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x) ፈርዖን ፡ ለዘመናት ፡ ሲያስጨንቅ ፡ ልጆችህን ሕዝቤን ፡ ልቀቅ ፡ ስትለው ፡ ትዕቢት ፡ አርጐ ፡ ሲፋንን በመጨረሻ ፡ ጌታ ፡ የግብጽን ፡ በኩር ፡ ገድለህ ህዝብህን ፡ ነጻ ፡ አውጥተህ ፡ ጠላትን ፡ . (1) . ፡ ጥለህ አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x) ሁልጊዜ ፡ ሃሳብህን ፡ የልብህንም ፡ ፈቃድ ታከናውነዋለህ ፡ በምትወደው ፡ መንገድ በጐና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው አምላካችን ፡ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ የምታደርገው አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x) ክብርህ ፡ ሰማያትንና ፡ ምድርን ፡ ሁሉ ፡ ሸፍኗል በምክርህ ፡ በመንገድህ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ያክልሃል ውበትህ ፡ ከፀሐይ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ይደምቃል ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይህን ፡ እያየ ፡ ያከብርሃል አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)