Loading
Singer
አቤቱ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x) ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x) አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ጌታ ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ኢየሱስ ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም (፪x) የተማመንኩብህ ፡ የነፍሴ ፡ አለኝታዬ ለሕይወቴም ፡ ዋስትና ፡ ሆነሃል ፡ ጌታዬ (፪x) መንፈሴን ፡ በሐሴት ፡ በደስታ ፡ ሞልተህ ያለ ፡ አንዳች ፡ ሥጋት ፡ ታኖረኛለህ ፣ ታኖረኛለህ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x) የውስጥ ፡ የልቤን ፡ በር ፡ በፍቅር ፡ አንኳኩተህ ክፈትልኝ ፡ ብለህ ፡ ፈቃዴን ፡ ጠይቀህ ፡ ወደ ፡ ልቤ ፡ ገብተህ ድካምሽን ፡ ስጭኝ ፡ እኔ ፡ ልሸከመው የሚል ፡ የልብ ፡ ወዳጅ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አየሁ (፪x) ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x) አቤቱ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x) ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ታምኛለሁኝ (፪x) አንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም (፪x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ጌታ ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ኢየሱስ ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም (፪x) መሸከም ፡ ቢያቅተኝ ፡ የሸክሙን ፡ ክብደት በፊትህ ፡ አስቀመጥኩት ፡ የጉድለቴን ፡ ብዛት (፪x) እርዳታህ ፡ ከሠማይ ፡ ሲመጣልኝ ፡ ድንገት የከበደኝ ፡ ሁሉ ፡ ተንሳፎ ፡ አየሁት (፪x) ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ጌታ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ (፪x)