Loading
ምን ፡ አቃተህና ፡ ማህተሙን ፡ ፈትተሀል ሰባቱን ፡ ጥቅል ፡ መጽሐፍ ፡ ልትከፍት ፡ ችለሀል እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ በማደሪያህ ፡ አለህ በዙፋን ፡ ላይ ፡ ሆነህ ፡ ሁሉን ፡ ታድሳለህ አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3 ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3 ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ጅማሬህ ፡ አይታወቅ ፡ ያንተ ፡ መጨረሻ ገደብ ፡ ልክ ፡ የሌለህ ፡ ሀያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በግርማ ፡ ሞገስህ ፡ ሁሉን ፡ የምትረታ አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል የሞትና ፡ የሲኦል ፡ መክፈቻ ፡ በእጅህ ፡ ነው በላይ ፡ ቢሆንም ፡ በታች ፡ ስልጣን ፡ ያንተ ፡ ነው አዶናዩ ፡ ጌታ ፡ ምንስ ፡ ይሳንሀል ቋጠሮውን ፡ ልትፈታ ፡ ብቻህን ፡ ችለሀል አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3 ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3 ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ በረከት ፡ እና ፡ ክብር ፡ ጥበብም ፡ ምስጋና ለታረደው ፡ በግ ፡ ይሁን ፡ ለዚያ ፡ ለገናና ሰቃይን ፡ እና ፡ ችግር ፡ መከራን ፡ ያስረሳ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የይኁዳ ፡ አንበሳ አቤቱ ፡ ውበትህን ፡ ማን ፡ ይመዝነዋል የዳዊት ፡ ስር ፡ እና ፡ ዘር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል በማደሪያህ ፡ ላይ ፡ አለህ (፫x) ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ በችሎትህ ፡ ላይ ፡ አለህ/3 ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.