Loading
Singer
በቃ ፡ አልፈልግም ፡ ልቤን ፡ ውሰደው አዕምሮዬን ፡ ግዛው ፡ ላአንተው ፡ አድርገው ዝም ፡ ልበልና ፡ ኃይልህን ፡ ልመልከት ሌላው ፡ ሃሣቤ ፡ ይብቃ ፡ ይከተት አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ? የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ የፍቅር ፡ አምላክ ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ ሌት ፡ በመኝታ ፡ እንዳስብህ ፡ አንተን ቀን ፡ በሥራዬ ፡ እንዳውጠነጥን ነህና ፡ ለነፍሴ ፡ ዕርካታና ፡ ደስታ ክብርህን ፡ ላስበው ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ? የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አድርጌ ፡ ተደነቅሁ ሥራህንም ፡ ሳየው ፡ በደስታ ፡ ተሞላሁ በዕውነት ፡ ተረዳሁ ፡ የአንተን ፡ ታላቅነት እንዲሁም ፡ አስተዋልሁ ፡ የእኔን ፡ ውዳቂነት አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ? የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ ለአንተ ፡ ሚገባህ ፡ ክብርን ፡ ለመስጠት በመንፈስ ፡ ሳስብህ ፡ ያኔ ፡ ተረዳሁት አሁን ፡ ቃል ፡ ኪዳኔ ፡ የመጨረሻው ተዋርጄ ፡ እንድኖር ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ ምሻው አዝ፦ አቤት ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ? እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ? የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለወጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ (፪x)