Loading
Singer
እውነትነቱን ፡ በመስቀል ፡ ላይ መቶ ፡ አለቃው ፡ ጌታዬን ፡ ቢያይ ተንበረከከ ፡ ሰገደለት ነካው ፡ የጌታ ፡ ቅንነት እንኳን ፡ አሁን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ አሸንፎአል ፡ ተንጠልጥሎ ሳያስፈራራ ፡ ሰው ፡ አንበርካኪ እንደእርሱ ፡ የለም ፡ ፍቅር ፡ ሰባኪ አቤት ፡ ደግነት ፡ ቸርነቱ ለሰው ፡ ያሳየው ፡ ምህረቱ (፮x) ፍቅር ፡ ምህረቱን ፡ የቀመሱቱ ውበቱን ፡ ያዩ ፡ ሐዋሪያቱ ስለእርሱ ፡ ኖረው ፡ መረጡ ፡ ሞት ለፍቅሩ ፡ ሆኑ ፡ ሰማዕታት ተነክተው ፡ በምህረቱ ተነክተው ፡ በቸርነቱ ነክቶአቸው ፡ ገርነቱ ነክቶአቸው ፡ የዋህነቱ የቱ ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ እጁን ፡ ያልሰጠ የሱስን ፡ አይቶ ፡ ያልደነገጠ ልከተልህ ፡ ያላለ ፡ ማነው የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ አሸናፊ ፡ ነው ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ስንቱን ፡ ማረከ በፍቅሩ ፡ አንበረከከ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እንጃ ወደደንው/ሰገድን ፡ያለ፡ ጠመንጃ (፪x) አቤት ፡ትህትና ፡አይ ፡ቅንነት ሰውን፡ ያስተማረ ፡ኖሮ ፡በሕይወት የሚሸጠውን፡ እግር ፡ ያጠበ ሩህሩህ ነው ጌታ፡ ፍቅር ፡ያነገበ ይህንን ፡ ጌታ ፡ የምትወዱት አስቲ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ኢየሱስን ፡ እንዲህ ፡ በሉት (፪x) እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፬x)