Loading
Singer
አቤት ፡ አምላኬ ፡ ያደገልኝን ፡ ሳስተውለው ፡ ባረኩህ (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያደረክልኝ ፡ ሳስተውሰው ፡ ወደድኩህ (፪x) ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው (፫x) ነፍሴን ፡ ያዳንካት ፡ ከጉድ ፡ ነው ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው (፫x) ነፍሴን ፡ ያዳንካት ፡ ከሞት ፡ ነው (፪x) የዘለዓለም ፡ ፍቅር ፡ የዘላለም ፡ ሕይወት ይሄው ፡ አሰጥቶኛል ፡ ወደ ፡ አብ ፡ መግባት ኢየሱስ ፡ አየሁት ፡ የፍቅርህን ፡ ልኩን አኔ ፡ አስገዝቶኛል ፡ እስከ ፡ ሞት ፡ መሆኑ ማንም ፡ ባያውቅህ ፡ የታወቅህ ፡ ነህ ማንም ፡ ባያምንህ ፡ የታመንህ ፡ ነህ እኔስ ፡ አውቄህ ፡ ሆንኩኝ ፡ ምስክር ሳላመነታ ፡ ሳልደናገር (፪x) እኔስ ፡ አውቄ ፡ ሆንኩኝ ፡ ምስክር ሳላመነታ ፡ ሳልጠራጠር ታሪክ ፡ ተረድቼ ፡ አይደለም ፡ ሲነገር ፡ ሰምቼ ፡ ብቻ ፡ አይደለም የሰራህልኝን ፡ አስቤ ፡ እከተልሃለሁ ፡ ከልቤ ታሪክ ፡ ተረድቼ ፡ አይደለም ፡ ሲነገር ፡ ሰምቼ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ያደረክልኝን ፡ አስቤ ፡ እኖርልሃለሁ ፡ ከልቤ አውቄያለሁ ፡ አውቄያለሁ ፡ ተረድቻለሁ የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ ሆኖ ፡ አግኝቼዋለሁ (፪x) አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ለኔ ፡ ማነው ማንስ ፡ ነው ፡ ልሙትልሽ ፡ ያለው ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ ያዳንከኝ ፡ አንተ ለዘለዓለም ፡ ልገዛልህ ፡ ላንተ ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ አድነህኛል የሰራህልኝን ፡ ልቤ ፡ አውቆታል ሳመልክህ ፡ በደስታ ፡ ሳከብርህ ፡ በደስታ ለነፍሴ ፡ በሞት ፡ ፈንታ ፡ መዳን ፡ አውጀሃልና (፪x) እንግዲህ ፡ ነፍሴን ፡ ካዳንክልኝማ በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ በደስታ ፡ ላንተ ፡ ጌታ በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ በደስታ እንግዲህ ፡ ነፍሴን ፡ ካዳንክልኝማ በውዴታ ፡ እገዛለሁ ፡ በውዴታ ፡ ላንተ ፡ ጌታ በውዴታ ፡ እገዛለሁ ፡ በውዴታ