Loading
Singer
አዝ፦ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ ሲገለጥ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ ሲታይ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ የኑሮዬ ፡ ለሊት ፡ እንዲነጋ ፡ የማውቅበት የሕይወቴ ፡ ለሊት ፡ ማዳኑን ፡ የማይበት (፪x) ዝም ፡ ባለው ፡ በድቅድቅ ፡ ለሊት ፡ አጋዥ ፡ በሚያሻበት ግራ ፡ ቀኝ ፡ እያየሁ ፡ ስጣራ ፡ ፈልጌ ፡ እረዳት አምላኬ ፡ መንፈሴን ፡ አንቅቶ ፡ አበራልኝ ፡ እውነቱን በከበበኝ ፡ ጨለማ ፡ መሃል ፡ አሳየኝ ፡ ምሕረቱን በሰማይ ፡ ያሉ ፡ ከዋክብት ፡ ሲመሽ ፡ እንደሚደምቁት ዙሪያዬ ፡ ሲጨልምብኝ ፡ የአምላኬን ፡ ማዳን ፡ አየሁት (፪x) አዝ፦ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ ሲገለጥ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ ሲታይ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ የኑሮዬ ፡ ለሊት ፡ እንዲነጋ ፡ የማውቅበት የሕይወቴ ፡ ለሊት ፡ ማዳኑን ፡ የማይበት (፪x) ሊያባብለኝ ፡ በምድረበዳ ፡ ወሰደኝ አስተምሮ ፡ አስተካክሎ ፡ ሊቀርፀኝ በውዴ ፡ ላይ ፡ በርሱ ፡ ብቻ ፡ ተደግፌ ይህች ፡ ማን ፡ ናት ፡ የሚሉኝን ፡ እንዳይ ፡ አልፌ ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ወዲያ ፡ ማዶ አሻገረው ፡ ብቻዬን ፡ ሊያይ ፡ ወዶ ሲታገለኝ ፡ ቆየ ፡ በጨለማው አስቸጋሪው ፡ ልቤን ፡ እስክረታው (፪x) ሥሜን ፡ ሊቀይር ፡ አድኖም ፡ ሊያስቀረኝ የሁለት ፡ ክፍል ፡ ሰራዊት ፡ ሊያረገኝ ሥርዓቱን ፡ እማር ፡ ዘንድ ፡ አስጨነቀኝ (፬x)