Loading
Singer
አቤት ምህረትህ እንዴት ታላቅ ነው መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ ነው እንደምን ታላቅ ነው ያንት ምህረት ከማን ጋር ይስተያይ ከፈጠርከው ፍጥረት ከምድር ወይ ሰማይ የሚስተካከልህ ማን አለ በውኑ አባቴ ምህረትህ ያክላል አንተኑ መለኪያ የለው መስፈሪያ የለው እንዴት ታላቅ (2X) ሳይታዘዝ ጠላት እጅ ገብቶ ሳምሶን ወደቀ ከመስመር ወጥቶ ግን ምህረት ለምኖ መቼ አፈረ የራሱ ፀጉር ማደግ ጀመረ በህይወት ከሰራው በሞቱ ባሰ ለዛ ኪዳን ሰው ምህረት ደረሰ አንድ ዕድል ብቻ ባይለምንህ ይኖር ነበረ በቸርነትህ እንዴት እንዴት እንዴት ታላቅ ነው (2X) እንዴት ኧረ እንዴት እንዴት እንዴት እንዴት ታላቅ ነው (2X) እንዴት ያንተ ምህረት አቤት ምህረትህ... ብትጨምርለት አስራ አምስት ዓመት ተዝቆ በማያልቅ ከሰፊ ምህረት ከኖረበት ዕድሜ ከምህረትህ ወስዶ አንተን ሳያከብር ጨረሰው በባዶ እኔንም ገብቶኛል የቃልህ ዕውነት ለካ ምዘምረው ባንተ ምህረት መሃሪነትህን እዘምረዋለሁ በጉልበቴ ሳይሆን በምህረት እኖራለሁ እንዴት... መለኪያ የለው...