Loading
Singer
አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው ላክብረው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x) አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x) እውነት ፡ የሆናቸው ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፪x) ሞገስ ፡ የሆናቸው ፡ ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፪x) አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x) በስራና ፡ በቃል ፡ ብርቱ ፡ የሆነው ፡ ጌታ እጃቸውን ፡ ይዞ ፡ ሁሌ ፡ እያበረታ ለዚህ ፡ ላበቃቸው ፡ ስንቱን ፡ እየመታ እዚህ ፡ አደረሳቸው ፡ ክፉን ፡ እየመታ ቃል ፡ የገቡት ፡ ቤተሰቦቹ (፫x) ከሁሉም ፡ ሚበልጥ ፡ አግኝቷል ፡ እጁ (፫x) ቃል ፡ የገቧት ፡ ቤተሰቦቿ (፫x) ወሰነች ፡ ልትኖር ፡ ከባሏ ፡ ብቻ (፫x) ቤተሰብ ፡ ጓደኛ ፡ ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ሁሉ በሰርጉ ፡ ያላችሁ ፡ ተጋባዥ ፡ በሙሉ ላጤነት ፡ አብቅቶ ፡ ብቸኝነታቹህ በቃ ፡ ለቀው ፡ ሄዱ ፡ ከቀድሞ ፡ ቀያቸው አመስግኑ (ኦሆ) ፡ አጨብጭቡ (አሃ) ለአምላካችሁ (ኦሆ) ፡ እልል ፡ በሉ (አሃ) (፪x) አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው/ላንግሰው ላክብረው/ላንግሰው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x) ከመጀመሪያው (፫x) እግዚአብሔር ፡ አንድን ፡ ወንድ ፡ ለአንድ ፡ ሴት ፡ አድርጐ ፡ ሰራው (፬x) ከመጀመሪያው (፫x) እግዚአብሔር ፡ አንድን ፡ ሴት ፡ ለአንድ ፡ ወንድ ፡ አድርጐ ፡ ሰራት (፬x) ይህ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ዛሬም ፡ ይህ ፡ ነው (፬x) ይህ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ዛሬም ፡ ይህ ፡ ነው (፬x) አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x) በስራና ፡ በቃል ፡ ብርቱ ፡ የሆነው ፡ ጌታ ሁሉን ፡ አሳመረ ፡ እጁ ፡ አለበት ይሄው ፡ አሳመረው ፡ ቃሉ ፡ አለበታ የቃል ፡ ኪዳን ፡ አምላክ ፡ ክንዱ ፡ አለበት አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x) እርሱ ፡ ያገናኘውን ፡ ሰው ፡ አይለየውማ ማጣመር ፡ ለሚችል ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዜማ ሰው ፡ ማድረግ ፡ ለሚችል ፡ ምሥጋናን ፡ ላሰማ መባረክ ፡ ለሚችል ፡ ዕልልታን ፡ ላሰማ ቃል ፡ የገቡት ፡ ቤተሰቦቹ (፫x) ከሁሉም ፡ ሚበልጥ ፡ አግኝቷል ፡ እጁ (፫x) ቃል ፡ የገቧት ፡ ቤተሰቦቿ (፫x) ወሰነች ፡ ልትኖር ፡ ከባሏ ፡ ብቻ (፫x) ቤተሰብ ፡ ጓደኛ ፡ ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ሁሉ በሰርጉ ፡ ያላችሁ ፡ ተጋባዥ ፡ በሙሉ ላጤነት ፡ አብቅቶ ፡ ብቸኝነታቹህ በቃ ፡ ለቀው ፡ ሄዱ ፡ ከቀድሞ ፡ ቀያቸው አመስግኑ (ኦሆ) ፡ አጨብጭቡ (አሃ) ለአምላካችሁ (ኦሆ) ፡ እልል ፡ በሉ (አሃ) (፪x) አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው/ላንግሰው ላክብረው/ላንግሰው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x)