Loading
Singer
አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፪x) አናልፈውም ፡ ብለን ፡ አለፍነውን ፡ የመከራው ፡ ዓይነት ፡ ብዙ ፡ ነው መች ፡ ተሸንፈን ፡ እናውቃለን ፡ አሸናፊዎች ፡ እንበልጣለን ይህ ፡ ያልፋል ፡ ብለን ፡ ያልገመትነው ፡ የእኛ ፡ ታሪካችን ፡ ብዙ ፡ ነው እያለፍን ፡ በድል ፡ ጐዳና ፡ አሸበረቅን ፡ በምሥጋና አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፪x) በሃሩር ፡ ጊዜ ፡ ሆኖ ፡ ጥላ ፡ በፍላጻ ፡ ሁሉ ፡ ከለላ ልጆቹን ፡ ፊት ፡ ፊት ፡ እየመራ ፡ ደርሰናል ፡ ጺዮን ፡ ተራራ የድካሙ ፡ ጊዜ ፡ አብቅቶ ፡ በብርታት ፡ ሕይወት ፡ ተተክቶ በሽብሸባ ፡ ፊቱ ፡ ዘለናል ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፡ ረድቶናል አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር አሁን ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያላችሁ ፡ አቤኔዘር ፡ የሆነላቹህ በፊቱ ፡ ቅረቡ ፡ በዕልልታ ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ከአመድ ፡ ከትቢያ ፡ ያነሳቹህ ፡ በዚህ ፡ ጉባኤ ፡ ስንቶች ፡ ናችሁ ታዲያ ፡ ለምን ፡ ነው ፡ ዝምታ ፡ የታል ፡ ደስታችሁ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር ይህ ፡ ያልፋል ፡ ብለን ፡ ያልገመትነው ፡ የእኛ ፡ ታሪካችን ፡ ብዙ ፡ ነው እያለፍን ፡ በድል ፡ ጐዳና ፡ አሸበረቅን ፡ በምሥጋና እንዲያ ፡ ሚከሰን ፡ ጠላታችን ፡ አሁን ፡ የታለ ፡ ከፊታችን ኢየሱስ ፡ ስለነገሠ ፡ በጠንካራው ፡ ክንድ ፡ ተደቆሰ አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፫x)