Loading
Singer
አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x) የደረሰበት ፡ ያውቃል ፡ ተስፋው ፡ የጨለመበት በቃ ፡ አለቀ ፡ ብሎ ፡ ሞቱን ፡ ሲጠባበቅ ድል ፡ በድል ፡ አድራጊው ፡ ጌታዬ ፡ ደርሶለት ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ያረገው ፡ ከላዩ ፡ ገፎለት (፬x) አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x) በምድረ ፡ በዳ ፡ ውስጥ ፡ አጋር ፡ እንዲያ ፡ ተጨንቃ ሲሞት ፡ እንዳታየው ፡ ልጇን ፡ አርቃ ፡ ጥላ ድምጿን ፡ አሰምታ ፡ በጣም ፡ አለቀሰች ማነው ፡ ሚደርስልኝ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ አለች እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ድምጻቸውን ፡ ሰማ የጨለመውን ፡ ሕይወት ፡ እንደገና ፡ አበራ (፬x) አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x) የሞት ፡ ፍርሃት ፡ መጥቶ ፡ ዙሪያዬንም ፡ ከቦኝ መሄጃ ፡ ማምለጫ ፡ ሁሉም ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ ተጨንቄ ፡ ሳለሁ ፡ ጌታ ፡ ደርሶልኛል ሸክሜን ፡ አራግፎልኝ ፡ በደስታ ፡ ሞልቶኛል (፬x) እንደሰው ፡ አይደለም (፰x) ይገርመኛል ፡ እዚህ ፡ መድረሴ (፪x) ይገርመኛል ፡ ሰው ፡ መሆኔ ይገርመኛል ፡ እኔ ፡ ማለፌ