Loading
Singer
የሲዖል ፡ ጣር ፡ ሲይዘኝ የሞት ፡ ወጥመድ ፡ ሲከበኝ ስማኝ ፡ ስለው ፡ አባባ ጩኸቴ ፡ ጆሮው ፡ ገባ ፡ አባባ አባቴ ፡ ቀንዴ ፡ ነው ፡ ረድኤቴ አባባዬ ፡ አባባ ፡ ጩኸቴ ፡ ጆሮው ፡ ገባ ፡ አባባ እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባዬ (፪x) ትምክህቴ ፡ ጦሬ ፡ ነው ፡ ጋሻዬ (፪x) ሰማይ ፡ ዝቅ ፡ አለ ፡ አምላኬ ፡ ወረደ (፪x) ከአፉ ፡ እሳት ፡ እየነደደ (፪x) ቁጣው ፡ ወጣ ፡ ጌታዬ ፡ በራ በቀል ፡ የእርሱ ፡ የአምላኬ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ ወየውለት ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ ወየውለት ፡ ዘመን ፡ መጣልኛ በአንተ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላላሁ በጭፍራው ፡ ላይ ፡ እሮጣለሁ አጥፋ ፡ ብሎኝ ፡ አውጥቶአቸው ቀስተ ፡ ሰይፉን ፡ አሳያቸው በቀኝህ ፡ አስር ፡ ሺህ ፡ ወደቁ ሳይቀርቡ ፡ ሺዎችም ፡ አለቁ እንደጋሻ ፡ እውነቱ ፡ ከበበኝ ከፍላፃ ፡ አስጣለኝ ሰማይ ፡ ዝቅ ፡ አለ ፡ አምላኬ ፡ ወረደ (፪x) ከአፉ ፡ እሳት ፡ እየነደደ (፪x) ኃይልን ፡ ለበስኩ ፡ አስታጠቀኝ የጠላቴን ፡ ጀርባ ፡ ሰጠኝ እንደ ፡ ጭቃ ፡ ረገጥኳቸው እንደ ፡ ትቢያ ፡ ፈጨኋቸው መክበቡን ፡ ዙሪያዬን ፡ ከበቡኝ አታልፍም ፡ ስንዝርም ፡ ብለውኝ በስቃያቸው ፡ ላይ ፡ እየሳቅኩ በሥምህ ፡ አሸነፍኩ ቁጣው ፡ ወጣ ፡ ጌታዬ ፡ በራ በቀል ፡ የእርሱ ፡ የአምላኬ ፡ የእርሱ ፡ ሥራ ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ ወየውለት ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ ለሚጠላኝ ፡ ወደረኛ ወየውለት ፡ ዘመን ፡ መጣልኛ